Desk note
Duty-free note requests require residence evidence and a complete goods inventory. The desk issues a support letter to Ethiopian Customs when documents are complete.
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ።
- አገልግሎቱን ለመጠየቅ አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል።
- በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም።
አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ፡-
- በኤምባሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ መሙላት
- ወደ ሀገር የሚያስገቧቸውን የግል መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር ማቅረብ
- የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመበት “Commercial Invoice” ማቅረብ
- የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመው ከዩኬ ውጪ ከሆነ፣ ግዢው በተፈፀመበት ሀገር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚሲዮን Commercial Invoice መረጋገጥ ይኖርበታል
- የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ ፓስፖርት ዋናው እና ኮፒ ወይም
- ፓስፖርት የሌላቸው ደግሞ ከኤምባሲ የተሰጠ የይለፍ ወረቀት/ሊሴፓሴ
- የብሪቲሽ መኖሪያ ፈቃድ /Resident permit or ID/ መሰረዙን የሚያረጋግጥ ሰነድ/ማስረጃ
ማስታወሻ ፡- ከላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች ተሟልተው ሲቀርቡ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል።





